Events

           ለሲዳማ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች የተላለፈ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
 
በኢፌዲሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1)፣ 393(2) እና 400 እንዲሁም በማህበሩ መመሥ ረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 21(1) እና 22(1) መሠረት 3ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎችን ቅዳሜ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም (November 30/2024) ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ኃይሌ ሪሶርት በሚ ገኘው ኦሎምፒክ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የተከበራችሁ ባለአክስዮኖች በእለቱ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪል አማካኝነት  በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

1. የአክሲዮን ማህበሩን የሚ መለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች፡
           1.1 ዋና መ/ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 892   ድረ-ገጽ:- www.sidamabanksc.com
           1.2 የምዝገባ ቁጥር:- MT/AA/10/0053062/2014
           1.3 የተፈረመ ካፒታል:- 1.4 ቢሊዮን
           1.4 የተከፈለ ካፒታል: 913 ሚ ሊዮን
2. የ3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-
        2.1. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚ ቴ አባላትን መሾም
        2.2. የተከናወኑ የአክስዮን ዝውውሮችን ማጽደቅና አዳዲስ ባለአክስዮኖችን መቀበል
        2.3. የዳይሬክተሮች ቦርድ እ.ኤ.አ 2023/2024 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥ ራ አፈጻጸም ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
        2.4. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ 2023/2024 በጀት ዓመት ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
        2.5. እ.ኤ.አ 2023/2024 በጀት ዓመት ዓመታዊ የተጣራ ትርፍ ድልድል ላይ ተወያይቶ መወሰን
        2.6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን እ.ኤ.አ የ2023/2024 በጀት ዓመት ዓመታዊ ክፍያ እና እ.ኤ.አ  የ2024/2025 በጀት ዓመት ወርሃዊ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን
        2.7. የቦርድ አባላት ምልመላና ሹመት ሥ ነ ሥ ርዓት ሰነድ ተወያይቶ ማጽደቅ
        2.8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ
        2.9. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ
3. የ3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-
        3.1 የማህበሩን መመሥ ረቻ ጽሁፍ ማሻሻል
        3.2 የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ
 
 4. ማሳሰቢያ 
         4.1 በጉባኤው ላይ በአካል የሚገኙ ባለአክሲዮኖችም ሆነ ወኪሎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ መያዝ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡
         4.2 በጉባኤው ላይ በአካል መሳተፍ የማይችሉ ባለ አክሲዮኖች አግባብነት ባለው አካል በተሰጠ ሕጋዊ ውክልና ወይም በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በአዲስ አበባ ከተማ ላንቻ አካባቢ ባለው ሚኪዎር ፕላዛ                       ሕንጻ ከሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥ 311 ወይም በሀዋሳ ከተማ ሂጣታ ቀበሌ አካባቢ በሚ ገኘው  የባንኩ ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ከህዳር 01-19/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመሙላት 
          በወኪል አማካኝነት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
 
ሲዳማ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ
ለተጨ ማሪ መረጃ፡-
የባንኩን ድረ-ገጽ፡ https://www.sidamabanksc.com ወይም
የፌስ ቡክ ገጽ፡http://www.facebook.com/sidamabanksc ይጎብኙ ወይም
በስልክ ቁጥር 011 470 4726 ወይም 046 220 6150 ይደውሉ
ሲዳማ ባንክ – በጋራ እንችላለን!
 

ሲዳማ ባንክ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው ኃይሌ ሪዞርት በሚያካሂደው 3ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫን ያካሂዳል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 9.3 መሠረት የምርጫ መስፈርቶች ከምርጫው አንድ ወር በፊት ለባለአክሲዮኖች መገለጽ እንዳለባቸው በሚደነግገው መሠረት የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ እጩዎችን በስብሰባው እለት መጠቆምና መምረጥ እንድትችሉ ለመላው የባንካችን ባለአክሲዮኖች ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ 

  1. ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባልነት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡ 
  2. 1. ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የባንኩ ባለአክሲዮን የሆነ እና የቦርድ አባል ሆኖ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
  3. 2. ዕድሜው 30 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፤
  4. 3. እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያለው፣
  5. 4. ከባንክ ሥራ ጋር ተዛማጅነት ባላቸው መስኮች በባንኪንግ፣ በሪስክ ማናጅመንት፣ ፋይናንስ፣ በአካውንቲንግ፣ በማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በሕግ፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ በኦዲቲንግ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት እና በዘላቂ ኢኮኖሚ እድገት ቢያንስ በአንዱ ዘርፍ 7 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው፤
  6. 5. በሌላ ባንክ ውስጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም ሠራተኛ ያልሆነ፣
  7. 6. በሌሎች ከአራት በላይ በሆኑ ተቋማት ውስጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ሆኖ በመሥራት ላይ ያልሆነ
  8. 7. ሀቀኛ፣ ታማኝ፣ ጠንቃቃ፣ እና መልካም ዝና ያለው እና በማጭበርበር፣ ዕምነት በማጉደል፣ ትክክለኛ ያልሆኑ የሒሳብ መግለጫዎች በማቅረብና በመሳሰሉት ተግባራት ተከሶ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ተሰጥቶበት የማያውቅ፣
  9. 8. በራሱ ወይም በሚመራው ወይም ዳይሬክተር በሆነበት ድርጅት ላይ የመክሰር ክስ ያልቀረበበት ወይም የኪሳራ ውሣኔ ያልተሰጠበት እንዲሁም በኪሳራ ምክንያት ንብረቱ ለዕዳ ማቻቻያ ያልተወሠደበት፤
  10. 9. በቂ ገንዘብ ሳይኖር ቼክ ሰጥቶ ሒሳቡ ያልተዘጋበት፤
  11. 10. ታክስ ባለመክፈል ተከሶ የጥፋተኛነት ውሳኔ ያልተሰጠበት፤
  12. 11. የባንክ ብድር ባለመክፈሉ ምክንያት ንብረቱ በሐራጅ ያልተሸጠ፣ተከሶ ያልተፈረደበት ወይም የሚመራው ወይም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይም የበላይ ኃላፊ የሆነበት ድርጅት ከገንዘብ ተቋማት የተበደረውን ገንዘብ ባለመክፈሉ ብድሩ ወደ ጤናማ ያልሆነ የብድር ደረጃ ያልዞረበት ወይም ያልገባበት፤
  13. 12. በጠቅላላ ጉባኤ እለት በሚቋቋመው ጊዜያዊ የቦርድ ጥቆማ እና አስመራጭ ኮሚቴ አባል የማይሆን
  14. 13. ሌሎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች እና በሕግ የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆን ይኖርበታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. 1. በወንድ ጾታ የተገለጸው ለሴት ጾታም ያገልግላል፡፡
  2. 2. በአጠቃለይ ከሚመረጡ የቦርድ አባላት 1/3ኛው ተጽኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ተጠቁመው በእነዚህ ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ፣ 1/3ኛው በሁሉም ባለአክሲዮኖች ተጠቁመው በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ሲሆን ቀሪ 1/3ኛው በነባር ቦርድ ተጠቁመው በሁሉም ባለአክሲዮኖች የሚመረጡ ገለልተኛ ዳይሬክተሮች (Indipendent Directors) ይሆናል፡፡
  3. 3. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ የሚካሄደው በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው፡፡
  4. 4. ቦርዱ በቂ የጾታ ስብጥር ያለው እንዲሆን ስለሚያስፈልግ ቢያንስ ሁለት ሴቶች በቦርድ አባልነት መመረጥ አለባቸው፡፡
  5. 5. ቦርዱ የትምህርት ዝግጅትና የሥራ ልምድ ስብጥር ያለው እንዲሆን ይፈለጋል፡፡ 6. ባለአክሲዮኖች ጥቆማ ሲሰጡ ስለአጩው ትምህርትና የሥራ ልምድ አጭር ማብራሪያ ለመስጠት መዘጋጀት አለባቸው፡፡
  6. 7. አንድ ባለአክሲዮን ራሱን በእጩነት መጠቆም ይችላል፡፡
  7. 8. መስፈርቶችን የሚያሟላ በሕግ ሰውነት የተሰጠው ተቋም/ድርጅት መመረጥ ይችላል፡፡ ነገር ግን ተቋም/ድርጅቱ ሲጠቆም ለተቋሙ/ድርጅቱ ቋሚ ወኪል ሆኖ የሚሠራ የተፈጥሮ ሰው በጥቆማው ሂደት መቅረብ አለበት፡፡
  8. 9. ከማህበሩ ጸሐፊ ውጭ ያሉ ሁለት የባንኩ ሠራተኞች ለቦርድ አባልነት ሊመረጡ ይችላሉ፡፡

ሲዳማ ባንክ አ.ማ – በጋራ እንችላለን!

ለተጨማሪ መረጃ፡- የባንኩን ድረ-ገጽ፡ https://www.sidamabanksc.com 

 የፌስ ቡክ ገጽ፡ http://www.facebook.com/sidamabanksc ይጎብኙ 

በስልክ ቁጥር 011 470 4726 ወይም 046 220 6150 ይደውሉ 

የማህበሩ ፀሐፊ