እንኳን አደረሳችሁ
በዛሬው ቀን በ2014 ዓ.ም የሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ወደ ባንክነት ለማሸጋገር የጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ስብሰባ በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎች የተላለፉበት ቀን ነበር::በዚህ ቀን የሲዳማ ባንክ ራእይ ተወለደ::
እነሆ አንድ ዓመት ሞላን::
በእነዚህ ጊዜያት የጠቅላላ ጉባኤው የሰጠውን ሀላፊነት በመጠቀም የተለያዩ ስራዎችን ቦርድ፣ ከፍተኛ አመራርና ሰራተኛው ሌት ተቀን በመረባረብ ሲሰራ ቆይቷል። የሚከተሉት ከተሰሩ ስራዎች በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፤
1. የጠቅላላ ጉባኤውን ቃሌጉባኤ ለብሔራዊ ባንክ በመላክ ማስመርመርና ማፀደቅ
2. የባንክ ምስረታ አማካሪ ጋር በርካታ ስራዎችን በመስራት ለብሄራዊ ባንክ ደብዳቤ በመላክ የቦርድ አባላትን ሹመት ማጸደቅ:
3. የባንኩን ፕሬዝዳንት ሹመት በብሄራዊ ባንክ ማጸደቅ
4. የም/ፕሬዝዳንቱን ሹመት በተመሳሳይ ማጸደቅ
5. ብሔራዊ ባንክ የጠቅላላ ጉባኤውን ቃለጉባዔ ካፀደቀ በኃላ ለ3 ወር ያህል የቆየ የባለአክሲዮኖች ፊርማ በውልና ማስረጃ ቢሮ ማስፈረም
6. በባለአክስዮኞች የተፈረመውን የውል መዝገብ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ
7. ብሔራዊ ባንክ የተፈረመውን የባለአክስዮኞች መዝገብ ከመረመረ በኃላ የስራ ፈቃድ ለማግኘት የሚያስችል በርካታ ስርዎችን መስራት
8. የባንክነት ሥራ ፈቃድ እ.ኤ.አ ሐምሌ 1/2022 ማግኘት
9.የብሄራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ በመቀበል ሎጎና ስም ማጸደቅ
10. በባንክ ሥራ ፈቃድ መሰረት በፌደራል ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ፈቃድ ማውጣት
11. በብሄራዊ ባንክ ፈቃድ መሰረት የግብር ከፋይ መዝገብ በባንኩ ስም መቀየር
12. በብሔራዊ ባንክ ህግና ደንብ መሰረት ቅርንጫፎችን በተለያዩ ቦታዎች ለመክፈት ቅድመ ሁኔታዎችን መስራት
13. ባንኩ የሚመራባቸውን የተለያዩ ፖሊሲና ደንቦችን በመቅረጽ ማስገምገምና ማጸደቅ
14. የተለያዩ የባንኩን አካውንት በብሄራዊ ባንክ ማስከፈት
15. የባንክ ሰራተኛ ቅጥርን ማከናወን
16. ነባርና አዳዲስ ሰራተኞች ክህሎትና ለማዳበር የተለያዩ ስልጠናዎች መስጠት
17.በብሄራዊ ባንክ ህግና ደንብ መሰረት ለዋና ቢሮ፣ ለእያንዳንዱ ቅርንጫፍ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ማሟላት
18. የኮር ባንኪንግ ሲስተም ግዥ በጨረታ የመግዛት ሂደት ስራዎች መስራት: ወዘተ
ቀሪ ጊዜያችንንም በመጠቀም በቴክኖሎጂ በመታገዝ የምንሰራቸው ስራዎችን የባንኩ ባለአክሲዮኖችና ደንበኞች በመጠባበቅ ላይ ያሉ በመሆኑ ከሚመለከተው አካል ጋር ሌት ተቀን ሰርተን ባንካችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን የምናደርግ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
የሲዳማ ባንክ ባለራእዮች እንኳን ደስ አላችሁ!
ሲዳማ ባንክ
የሁሉም ባንክ
መስከረም 22/2015 ዓ.ም