ለሲዳማ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች የተላለፈ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
በኢፌዲሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ 367(1)፣ 393(2) እና 400 እንዲሁም በማህበሩ መመሥ ረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 21(1) እና 22(1) መሠረት 3ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎችን ቅዳሜ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም (November 30/2024) ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ ኃይሌ ሪሶርት በሚ ገኘው ኦሎምፒክ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም የተከበራችሁ ባለአክስዮኖች በእለቱ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪል አማካኝነት በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1. የአክሲዮን ማህበሩን የሚ መለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች፡
1.1 ዋና መ/ቤት አድራሻ፡- አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 892 ድረ-ገጽ:- www.sidamabanksc.com
1.2 የምዝገባ ቁጥር:- MT/AA/10/0053062/2014
1.3 የተፈረመ ካፒታል:- 1.4 ቢሊዮን
1.4 የተከፈለ ካፒታል: 913 ሚ ሊዮን
2. የ3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-
2.1. የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና አስመራጭ ኮሚ ቴ አባላትን መሾም
2.2. የተከናወኑ የአክስዮን ዝውውሮችን ማጽደቅና አዳዲስ ባለአክስዮኖችን መቀበል
2.3. የዳይሬክተሮች ቦርድ እ.ኤ.አ 2023/2024 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥ ራ አፈጻጸም ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
2.4. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ 2023/2024 በጀት ዓመት ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
2.5. እ.ኤ.አ 2023/2024 በጀት ዓመት ዓመታዊ የተጣራ ትርፍ ድልድል ላይ ተወያይቶ መወሰን
2.6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን እ.ኤ.አ የ2023/2024 በጀት ዓመት ዓመታዊ ክፍያ እና እ.ኤ.አ የ2024/2025 በጀት ዓመት ወርሃዊ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን
2.7. የቦርድ አባላት ምልመላና ሹመት ሥ ነ ሥ ርዓት ሰነድ ተወያይቶ ማጽደቅ
2.8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ
2.9. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ
3. የ3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-
3.1 የማህበሩን መመሥ ረቻ ጽሁፍ ማሻሻል
3.2 የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ
4. ማሳሰቢያ
4.1 በጉባኤው ላይ በአካል የሚገኙ ባለአክሲዮኖችም ሆነ ወኪሎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ መያዝ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡
4.2 በጉባኤው ላይ በአካል መሳተፍ የማይችሉ ባለ አክሲዮኖች አግባብነት ባለው አካል በተሰጠ ሕጋዊ ውክልና ወይም በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በአዲስ አበባ ከተማ ላንቻ አካባቢ ባለው ሚኪዎር ፕላዛ ሕንጻ ከሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥ 311 ወይም በሀዋሳ ከተማ ሂጣታ ቀበሌ አካባቢ በሚ ገኘው የባንኩ ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ከህዳር 01-19/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመሙላት
በወኪል አማካኝነት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ሲዳማ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ
ለተጨ ማሪ መረጃ፡-
የባንኩን ድረ-ገጽ፡ https://www.sidamabanksc.com ወይም
የፌስ ቡክ ገጽ፡http://www.facebook.com/sidamabanksc ይጎብኙ ወይም
በስልክ ቁጥር 011 470 4726 ወይም 046 220 6150 ይደውሉ
ሲዳማ ባንክ – በጋራ እንችላለን!